Songtexte.com Drucklogo

Marakiye Songtext
von Teddy Afro

Marakiye Songtext

በምሥራቅ ፀሀይ ወጥቶ እሲፈካ ሠማይ
ካንሶላው ገብቼ እኔ አልተኛም ብታይ
በናፍቆትሽ እምባ እየራሰ አልጋዬ
ካላንቺ አቅቶኛል ማደር ለብቻዬ

ማራኪዬ ማራኪዬ
አንቺ የልቤ ጉዳይ
መልክሽ ሁሌም ካይኔ ላይ ነው
ሌትም ቀንም ብታይ

ማራኪዬ ማራኪዬ
አንቺ የልቤ ጉዳይ
መልክሽ ሁሌም ካይኔ ላይ ነው
ሌትም ቀንም ብታይ

ማርኮ መማር ነበር የጀግና ሞገሱ
ከሩቅ አስረሽ ልቤን የት ያምልጥ ከራሱ
የጎደለው ከአርባ (40) ስንት ይሆን እጣዬ
ካልንቺ አልሞላ አለኝ እርጂኝ ማራኪዬ


ማር ማር ይላል ሁሌ አፌ ሲጠራሽ
ማር ማር ይላል እያቆላመጠ
ማር ማር ይላል አይኖር ያላንቺ
ማር ማር ይላል እድሜ እየጣፈጠ

መች ጠገብኩሽ እና እኔ
ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ፀንቶ ብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ሥራዬ

መች ጠገብኩሽ እና እኔ
ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ፀንቶ ብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ሥራዬ

ማራኪዬ ማራኪዬ
አንቺ የልቤ ጉዳይ
መልክሽ ሁሌም ካይኔ ላይ ነው
ሌትም ቀንም ብታይ

ማር ማር ይላል ሁሌ አፌ ሲጠራሽ
ማር ማር ይላል እያቆላመጠ
ማር ማር ይላል አይኖር ያላንቺ
ማር ማር ይላል እድሜ እየጣፈጠ


መች ጠገብኩሽ እና እኔ
ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ፀንቶ ብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ሥራዬ

መች ጠገብኩሽ እና እኔ
ሌት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ፀንቶ ብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ሥራዬ

ማር
ማር ማር
ማር
ማር ማር
ማር ማር ይላ... ል ይላል
ማር ማር ይላ... ል

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Teddy Afro

Quiz
Wer will in seinem Song aufgeweckt werden?

Fans

»Marakiye« gefällt bisher niemandem.