Songtexte.com Drucklogo

Alew Neger Songtext
von Lij Michael

Alew Neger Songtext

ባቲ ባቲ ባቲ ባቲ

አለዉ አለዉ ነገር አለዉ ነገር
የኔ እና ያንቺ ነገር
አለዉ አለዉ ሰላም አለዉ ሰላም
የኔ እና ያንቺ አለም
አለዉ አለዉ ነገር አለዉ ነገር
የኔ እና ያንቺ ነገር
አለዉ አለዉ ሰላም አለዉ ሰላም
የኔ እና ያንቺ አለም


ከማማርሽ ጋር ተሸምኖ
ያገሩ ቅኝት ስምሽ ሆኖ
ብለዉ ከጠሩሽ እቴ ባቲቱ
ወዲህም አንቺዉ ነሽ ወዲህም ቅኝቱ
አንቺ ቆንጆ የሎሚ ሽታ (ሽታ ሽታ)
መጣዉ ጠብቂኝ አልቀርም ማታ (ማታ ማታ)
ውሰደኝ እግሬ ድረስ እዛ
የምቀር መስሏት እንደዋዛ
አይታኝ እየሮጠች ገባች ትዛዝ አዛ
አይመጣም ብላ ከሸገር እዛ
ሁሉም እሷን እሷን እሷን ይመኝሽ
ቢጥመው ነዉ መሰል ሰም እና ወርቅሽ
ተጉዞ ደራሹ ሳይመሽ እጋ
ስንቱ ቤትሽ ቀረ ዉበትን ፍለጋ
ዉሰዳት ይሉኛል ወዴት ልዉሰድሽ
የመዉደድን ነገር ማን አወቀልሽ

አዉሬ ማደንዘዣ አብነት ድምፅሽ
ያደመጠዉ ሁሉ ሲታመምልሽ
ለወሬም ነጋሪ አንድ አልቀረልሽ
የሴቱን አናውቅም ወንድ አለቀልሽ

ኧረ ባቲ ባቲ
ባቲ ገንደልዩ
ሀድራው የሚሞቀው
ኧረ ባቲ ባቲ (ባቲ ባቲ)
ባቲ ልዩ ዜማ (ባቲ ባቲ)
ሲባዝተዉ ያድራል (ባቲ ባቲ)
ፍቅርን እንደሸማ (ባቲ ባቲ)
ኧረ ባቲ ባቲ (ባቲ ባቲ)
ባቲ ሀገሩ መላ (ባቲ ባቲ)
ስወደዉ አድራለዉ (ባቲ ባቲ)
ያንቺንማ ገላ (ባቲ ባቲ)


በባቲ መንገድ በቀጭኑ
ጉብል ለጉድ ነዉ በየቀኑ
ዉሰዱኝ እና ከመንደሩ
እኔም ይድረሰኝ ወግ ሀገሩ
በባቲ መንገድ በቀጭኑ
ጉብል ለጉድ ነዉ በየቀኑ
ዉሰዱኝ እና ከመንደሩ
እኔም ይድረሰኝ ወግ ሀገሩ

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Lij Michael

Quiz
Welche Band singt das Lied „Das Beste“?

Fans

»Alew Neger« gefällt bisher niemandem.