Songtexte.com Drucklogo

Alew Belegn Songtext
von Teddy Yo

Alew Belegn Songtext

አ እሺ ልጅ እያሱ
Jungle productions
ችግር ችግርን ሲወልድ
ጭንቀቱ ሲደራረብ
ረሀብ ሲጠናብኝ
ተተብትቤ በሱስ መረብ
የልጅነት ህልሜ
እንደጉም ሲበታተንተን
አለሁ በለኝ ጌታዬ
እኔን አለሁ በለኝ ወገን
ፊቷን ስታዞርብኝ
ያደኩባት መሬት
የአብሮ አደግ ተመፅዋች መሆን
ይመራል እንደ ሬት
የማይቻል የለም
ይሄንንም ልቻል መቼስ
ዘመድ የለኝ የሚመለከተኝ
እኔን ዞሮ
ታላቅ እህቴ ቡና ቤት
ወንድሜ ሊስትሮ
ሲርበኝ አድራለሁ ቆርጥሜ
የ አስር ሳንቲም ቆሎ
ጌታ ካላለፈልኝ ውሰደኝ አሁን ቶሎ
የትኛው ሰው ጆሮ ሰቶ
ሰማ የኔን ሮሮ
የጪስ መአት ሲጎርፍበት
ከደረቀው ጉሮሮ
እህ ዘላለም ተማሮ
ህይወት መተንፈስ ሆነና
ይህም ተባለ ኑሮ


አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ
አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ

ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት
ደመና ፊቱን ሲያጨልም
መጣሁ ቀረሁ እያለ
ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም
ሆዴን በባዶ ይዤ
ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም
አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ
ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት
ደመና ፊቱን ሲያጨልም
መጣሁ ቀረሁ እያለ
ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም
ሆዴን በባዶ ይዤ
ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም
አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ

አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ
አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ

ጎህ ሲቀድ በማደሬ ስረጋጋ
የያዝኩትን ነጥቆ በላ ከመንጋጋ
በየምግብ ቤቱ ስዞር
ሚቀመስ ፍለጋ
ስገረፍ ውላለሁ በረሀብ አለንጋ
ጡቷ ደርቆባት እናት
ሲንሰቀሰቅ ልጇ
ሁሉን ስትማፀን ዛሬ
ተዘርግቶ እጇ
በሀዘን ስታነባ ሁሌ
ጠፋና ወዳጇ
ጌታ አየዋለሁ በለኝ
በጭንቅ ባማላጇ
በሚቆረጥም ብርድ ላይ
በጎዳና ብወለድም
አጥቼ እንጂ የሚሰማኝ
ብዬ ነበር አልወለድም
ቅንጦት ያሰቃየው
ቢበዛባት በዚች አለም
ለቀበጠቺው ሁሌ ያድራል
ደሞ ሲሸላለም
ልመናን አልፈልግም
የሰው ኪስን ቧጦ
ፍላጎቴ መለወጥ ነው
ሰርቶ ማደግ ሮጦ
ማየት እፈልጋለሁ
ህይወት ተለውጦ
አሁን ምኖረው ኑሮ
ታሪክ ተገልብጦ

አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ
አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ

ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት
ደመና ፊቱን ሲያጨልም
መጣሁ ቀረሁ እያለ
ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም
ሆዴን በባዶ ይዤ
ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም
አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ
ፀሀይ ጉልበት ሲከዳት
ደመና ፊቱን ሲያጨልም
መጣሁ ቀረሁ እያለ
ዝናብ ድምፁን ሲያስገመግም
ሆዴን በባዶ ይዤ
ወደ ጎዳና ቤቴ ሳዘግም
አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ
ዝናብ ቤቴን ሲያፈርሰዉ
ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ
ለማን እከሰዋለው
ማን አዛዥ የለው እሱማ
ነገን ማሰብ አቁሚያለሁ
ተስፋዬ ደብዝዞ
የኔ መከራ እንደው አያልቅ
እንደዋዛ ተመዞ
መቼ ነው እንደሰው ምኖር
እንደወፍ መኖር ትቼ
የዛሬን ብቻ ሳይሆን
የነገንም አስልቼ
አለሁ በለኝ አይሁንብኝ
ጌታዬን መፈታተን
የጎዳና ልጆችህን
በቅዱስ እጅህ ባርከን

አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ
አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ
አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ
አለሁ በለኝ ጌታዬ
በቃ በለኝ ጎዳና አለሁ በለኝ ጌታዬ
አለሁ በለኝ በቃ በለኝ

አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ
አንተ አለሁ በለኝ

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Teddy Yo

Fans

»Alew Belegn« gefällt bisher niemandem.